Monday, December 31, 2012

በክርስትና ይቅርባይነት ሁለቴ የሚታሰብበት ተግባር አይደለምለቤተ ክርስቲያንና ለክርስትና ልዩ ፍቅር እንዲያድርብኝ ያደረጉኝና በቃልም በሕይወት ያሰተማሩኝ ሰዎች ጥቂት የሚባሉ አደሉም ከነሱ መካከል ግን ትዝታቸው ሁል ጊዜ የማልረሳቸው የሰሜን ጎጃም ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት እና ከጥቂት አመታት በፊት ያረፉት አቡነ በርናባስ ናቸው:: በካንፓስ በነበረኝ ቆይታ ተማሪዎችን በእምነታቸው በማጽናትና የመንፈስ አባት በመሆን ታላቅ ሥራ የሰሩ አባት ነበሩ። እሳቸው ክርስትንና በቅዱሳን እምነት ስለቤተ ክርስቲያን ደግም በግብረ ቅዱሳን ምስክርነት ያስተምሩን ትዝ ይለኛል:: ካሰተማሩኝና በታሪኳም ቤተ ክርስቲያን ብዙ ፈተናዎች እና ተግሮቶች አሳልፋላች::ተወጥታለች::ይህ የሆነው በእግዚአብሔር ሃይል ቢሆንም የቤተ ክርስቲያን ልጆች እና አገልጋዮች ፈተናው በሚጠይቀው ዋጋ መጠን ስለከፈሉ ነው።ሕይወት እሰከመስጠት::

ፓትሪያርክ አቡነ  ጰውሎስ ካረፉ 5 ወር ሊሞላ 2 ሳምንት ቀርቷል:: በዚህ ወቅት በቤተ ክርስቲያን አባቶችም በአገልጋዮችም በምዕመኑም ዘንድ ሲታስብ የቆየው የቤተ ክርስቲያኗ አባቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው። ይህም የሆነበት ምክኒያት ይህንን ችግር አሁን መፍታት ካተቻለና ወደ ፊት መፍትሄ ወደማይገኝለት ደረጃ እንደሚደርስ ስለሚታመን ነው።  ይህ ያሳሳባቸው ሁሉ በየበኩላቸው ብዙ ሲጣጣሩ ቆይተዋል:: ከመቸውም በላይ በነዚህ ጥቂት ወራት ወስጥ የእርቀ ሰላሙን አስፈላጊነት የሚያሳስቡ (ግድ የሚሉ) ብዙ መልእክቶች/ጽሁፎች ተጽፈዋል::በተለያዩ መንገዶችም  አገልጋዩና ምዕመኑ ድጋፉን ስገጽ ቆይቷል::
here