Tuesday, February 21, 2012

የዲያስጶራው ወሬ 1: የቤክአችን ትርምስ

ኢቲቪ ብቻ መስሏችሁ ጉድ የሚያወራው እንዳትሸወዱ በዲያስፖራው ያሉ ወሬዎችን ላካፍላችሁ ግድ ይለኛል።
እዚህ በሰሜን አምሪካ (ዲሲና አካባቢውየምንሰማው ወሬ ቀላል አይምሰላችሁ። የአሁኑ የፆም  መያዣ   የ"ዘወረደ" አለት እሁድ ግን የነበረው ትንሽ ለየት ያለ ነበር። ነገሩ እንዲህ ነው
ለቤተ ክርስቲያኗ ቀኖናእና ሕጎቿ  ዋሪያዊት ሚያደርጓት መሠራቶች ሆኖው ሳለ እዚህ አገር በቆየሁባቸው 6 አመታት ግን ሰዎች፣ የቤተ ክርስቲያን አባቶች/ሃላፊዎችና ተቆርቋሪ የሆኑ ምዕመናን በሚያነሷቸው ምክንያቶች/ሰበቦች እና በሚይዟቸው አቋሞች ይህ ስርዓተ ቤት ክርስቲያን በቀላሉ ሲጣስ፣ሲሻር ይቻለሁ።በዚህም ምክንያት በዲሲና አካባቢው ያሉ አቢያተ ክርስቲያናት በሐይማኖት ኦርቶዶክሳዊ ከመሆን ውጪ በአስተዳደራዊ ስርዓት ፍጹም የተለያዩ ሆነዋል።ይህ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኗን ብቻ አይደለም ምዕመኑ ራሱ በአቋምም በማህበራዊ ሕይወትም እንዲለያይ አድርጎታል  
በዚህ ሳምንት ግን ለያዙት አቋም እና አንድነት ወይም ከፋፈል መለያ ምልክት ሆኖ የቆየው ስም  የመጥራት ጉዳይ ደርጃውን ትንሽ ከፍ መልኩን ትንሽ ለወጥ አደርጎ ነበር የዋለው። የተለመደው አካሄድ በእናት(በቅዱስ ሲኖዶስ ስር ያሉቤተ ክርስቲያን ስር ያሉ የፓትሪያርኩ ስም እና የሊቀ ጳጳሱን ስም ይጠራሉ፣ በስደተኛ ሲኖዶስ ሥር ያሉት ደግሞ የአቡነ መርቆሪዮስን ስም ይጠራሉ በሁለቱን አንመራም ያሉ ወይም ገለልተኛ ተብለው የሚጠሩት ደግሞ የአጥቢያውን የበላይ ጠባቂ ይጠራሉ። ክፍፍሉ በዚህ አያበቃም። የአገሪቱ ሕግ ስለሚፈቅድ/ሰለሚያስገድድ እና አቢያተ ክርስቲያናቱም እራሳቸው ቀድሞውኑ ቋቋሙ  ይም በአገሩ ቋንቋ ከፈቱ በአቶ  በአባ  ወይም በወ/  በጎ ፈቃድ ሰለሆነ ንብረትነቱም  ለእነ ኤቢሲ ይሆናል።ቤተ ክርስቲያኗ ወስጥ የሚደረገው ሁሉ የሚቆጣጠሩ እነዚሁ ሰዎች ናቸውና።
ሰለዚህ አንድ በዲሲ አካባቢ ያለ ቤት ክርስቲያን ብንወስድ ከእነዚህ 8 አይነት አቋሞች ውጪ አይሆንም።
1.
ኖዶስን የሚቀበል ፓትሩያርኩን የሚቀበል ሊቀ ጳጳሱን የሚጠራ
2. 
ኖዶስን የሚቀበል ፓትሩያርኩን የሚቀበል ሊቀ ጳጳሱን የማይጠራ አቡነ ማቴያስን የሚጠራ
3. 
ሲኖዶስን የሚቀበል ፓትሩያርኩን የሚቀበል ሊቀ ጳጳሱን የማይጠራ አቡነ ገብራኤልን የሚጠራ
4. 
ኖዶስን የሚቀበል ፓትሩያርኩን የሚቀበል ሊቀ ጳጳሱን የማይጠራ አቡነ አብርሃምን የሚጠራ
5. 
ኖዶስን የሚቀበል ፓትሩያርኩን የሚቀበል ሊቀ ጳጳሱን የማይጠራ 
6. 
ኖዶስን የሚቀበል ፓትሩያርኩን የማይቀበል ሊቀ ጳጳሱን የማይጠራ የደብሩን አለቃ የሚጠራ
7. 
ኖዶስን የሚቀበል ፓትሩያርኩን የማይቀበል ከአቡነ ፈኑኤል በስተቀር ሌላ ሊቀ ጳጳስ የማይጠራ
8. 
ኖዶስን የማይቀበል ፓትሩያርኩን የማይቀበል ሊቀ ጳጳሱን የማይጠራ - ስደተኛ

ይህ ሁሉ እንግዲህ በክርስቶስ አንድ የሆንን የአንድ ቤተክርስቲያን ልጆች መሃል የተፈጠረ ነው።  በየአቢያተ ክርስቲያናቱ ያሉት አስተዳዳሮች ደግሞ የያዙት አቋም እንዴት ትክክለኛ እንደሆነ ሲያስተምሩን ሃይማኖታዊ ምክንያት ሲሰጡን የሌሎቹ ስህተት መሆኑን ሲሰብኩን ኖረዋል። እኛም አምነን ተስማምተን ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት “እየጸለይን” ወይ እነሱም ጸልዩ አሜን እያልን ለሌሎቹ ማለትም እኛ የምንሄድበት ቤተ ክርስቲያን የማይሄዱና አሰተዳደራዊ መመሳሰል ለሌለን አምላክ ልቦና እንዲሰጥልን እየለመንን ኖረናል። ታዲያ የአሁኑ እሁድ እንዲህ ሲሆን ውሏል
አስተዳደር 7 የፓትሩያርኩን ስም ጠራ ይህ ማለት ደግሞ አስተዳደር 7 እና አስተዳደር 1 አንድ ሆኑ ማለት ነው
አስተዳደር 6 የሊቀ ጳጳስ ስም ጠራ ይህ ማለት ደግሞ አስተዳደር 7 እና አስተዳደር 6 አንድ ሆኑ ማለት ነው
አስተዳደር 5 የሊቀ ጻጻሱ ስም ጠራ ይህ ማለት ደግሞ አስተዳደር 1 እና አስተዳደር 5 አንድ ሆኑ ማለት ነው
አስተዳደር 3 የሊቀ ጻጻስ ስም ጠራ ይህ ማለት ደግሞ አስተዳደር 2 እና አስተዳደር 3  አንድ ሆኑ ማለት ነው
ከዚህ የምንረዳው አንድ ነገር አለ። ለእርቀ ሰላም ወይም ለቤተ ክርስቲያኗ አንድነት ዋነኛ ተጠያቂዎችና ኃላዎች የቤተ ክርስቲያዋ አባቶች ናቸው። እንደዚህ ከፋፍሎን ያለን የስም መጥራት ጉዳይ ቢጠሩ መሬት እንደምትሰበር አድርገው አስተምረውን ሲያበቁ እንዲህ በቀላሉ ሲጠራሩ ለዋል። ታዲያቤተ ክርስቲያንን እንዲህ ከፋፋሏት እና ለሀዛኑ መጽናኛ ከመሆን ይልቅ የሀዘኑ ምክንያት የሆነችበትን ምዕመን በማህበራዊ ሕይወቱ ራሱ እንዲለያይ ያደረጉበት ምክንያንት እንደቀላል መሻር ከቻሉ ቀድሞውኑ ተጣልተው ነበር የሚለውን ማመን ይከብዳል። እንደ እኔ እንደ እኔ መክበድ ብቻ አይደለም አለተጣሉምም። በዚህ ሁሉ  ብዙ ጥያቄዋች ተፈጥረውብኛል
 1. ካልተጣሉ ለምን ይከፋፍሉናል ?
 2. ተጣልተውም ከሆን እርቅ እንዲህ ቀላል ከሆነ ለምን አይታረቁም ?
 3. እንዲህ እንደልባቸው ለሚገሩት ምዕመን ለምን ያለኃጢእያቱ ኃጢእያት ያሸክሙታል ?
 4. ለምን ያልተደረገ ታሪክ ተረት ተረት ይነግሩናል ? ከሁሉም በላይ ደግሞ 
የሚያሳስበኘ ቤተ ክርስቲያኗ አባቶች ነገሩ አንደፈለጉ ሲያሰፉ ሲያጠቡ ሳይ ለራሳቸው የስልጣን ምኞት አና ጥቅም አለመሆኑን ለማመን እቸገራለሁ። መቸገር ብቻ አይደለም አባቶቼን የማምንበት የዋህነት እያጣሁኝ ነው።  ይህን ሊመልሱልን መቻላቸወነም እጠራጠራለሁ :: ይመልሱልን ይሆን ?   
ጥያቄ የማይሆንብኝ በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ አማናዊቷ ቤተ ክርስቲያን አትከፋፈልም የእኛ የሰዎች ሃሳብ እንጂ። እግዚአብሔር አምላክ እንደ እዮብ ቆም በለን ተአምራሩቱን  እንድናስብ እና የኛ ሳይሆን የእርሱ ሃሳብ እንዲከናውን መልካም ፈቃዱ ይሁንልን።አሜን።
እስኪ እነምከርበት