Tuesday, January 31, 2012

ትንሿ ጎጆህን


የሚያስመካ ዘመድ
የክፉ ቀን ደራሽ
----ሲቸገሩ የማይወድ
ለተበደሉ የሚክስ
ለሆዱ አድሮ
----ሕግን የማያፈርስ
እውነትን አትልቀቅ
ይልቁንም በርታ
----እምነትህን አጥብቅ
የሚልህ ቢጠፋ
የሚሰጥህ ተስፋ
ለሰው ለሰው እኔ አለሁ የሚልህ
የሕግ ሰው ቢሆን የሚሰጥህ ፍትህ
ሁሉም ቢሸሽ
ፍትህ እና ሰው እየራበህ
----ነግቶ ቢመሽ
ቀቢጸ ተስፋ ቀርቦህ
ሀዘን ሙቀት ቢሆን ለትንሿ ጎጆህ
አንዲት ነገር አስታውስ
ያኔ በልጅነት
----የተቀበልካትን እንድትሆንህ ፈውስ
ያችን የተሰፋ ቃል
ሰፍራ ያገኘሃት ተጽፋ በውንጌል
በልብ ተከትባ ታትማ እንድትኖር
እንድትሆንህ ስንቅ ከሀዘን መውጫህ በር
ሁሌ እንድታጽናናህ ተነግራህ የነበር
መርታ የምታበቃህ ለታላቅ ልዩ ክብር

ውስጥ ባኖረ በአምላክህ ልዩ ሀይል
ማርቆስ በጻፈልህ እንዲሁ በወንጌል
በሦስት ምርጥ ቃላት
ሁሉን ሊያስችልህ
----አምላክ ቃል የገባበት
የነገር ሁሉ ፍጻሜ
የፍርሃት የጭንቀት የሁሉ ድምዳሜ
ለካሁሌም በውስጥህ ናት
የመቻልህን መጠን የምትለካባት
ስለዚህ እንዲህ ብሏል
“ለሚያምን ሁሉ ይቻለዋል”
ሀዘን እና ችግር እንዳያናውጣት
ትንሿ ግጆህን በዚህ ላይ አንጻት 

Monday, January 9, 2012

ትዝታ

ፖሊ እያለሁ አሁን አሁን ሁል ጊዜ ትዝ የምትለኝ ትዝታ የምትባል አንድ ትንሽ ልጅ ነበች። የተማሪዎች የራት መመገቢያ ሰዓት ሊያበቃ ሲል ካፌው አካባቢ ብቅ ብቅ ከሚሉትና ከተማሪ የሚተርፈውን ምግብ ተስፋ እያደረጉ ከሚኖሩት ተስፈኞች አንዷ ናት። ትዝታ ግን እራሷን ለማማሻሻል ሁል ጊዜ ጠረት የምታደር ሰለነበረች ከትምህርት ቤተ በኋላ ያላትን ሰዓት ትንሽ ሽርፍራፊ ሳንቲም ለማግኘት ለተማሪዎች ትላላክ ነበር። ቆየት ብሎ በእነ Abdi Zeynu, Weineshet Lakew , Solomon Yishak, Abiy Mekonnen Girum Kassa, Waleligne Cherinet Yohannes Samuel የተስፈኞች ልጆችን ለመርዳት የተቋቋመው RDL (Redefining Life) ለትዝታ የሊስትሮ ሳጥን ገዝቶላት በዛ የተሻለ ሳንቲም እያገኘች እራሷንም ወንድሟንም እናቷዋንም ትረዳ ነበር።

ትዝታ ጠዋት ትምህርት ቤት ከሰዓት ደግሞ የሊስትሮ ሳጥኗን ይዛ ወንዶች እና ሴቶች ዶርም መሃል ያለችው ዛፍ ስር ቁጭ ብላ የተማሪዎች ጫማ ትጠርጋለች፣ ሥራ ደግሞ ቀዝቀዝ ሲል የምትላከው ካለ ወደ ዶርሞቹ ጎራ ትላላች ማታ ደግሞ ወድ ካፌ ሮጣ ለእሷና ለቤተሰቦቿ የሚሆን ቡሌ ትቀበላለች ከዛ በኋላ ደግሞ ከካምፓስ ጊቢ መውጫ ሰዓት እስኪደርስ የመምህራን ላውች መሄ ለደበረው ስትላላክ ታመሻለች።

አንድ ቀን ችከላ ደብሮት ሰራ መፍታት የፈለገ አንድ ተማሪ ጫማውን እሷ ጋር ያሰጠርጋል፣ ልጁ ድብርቱን ለመርሳት ይሁን ወይ ሰለሷ ለማውቅ ካለው ጉጉት ትዝታን ብዙ ጥያቄ ይጠይቃታል፣ የቻለችውን ትመልሳለች ያልቻለችውን ደግሞ አላውቅም ትላለች ልጁ አላውቅም ላለችው ነገር ሁሉ ረጅም መሃንዲሳዊ ማብራሪያ ይሰጣታል ከጨራሰ በኋላ ደግም “አሁንስ ገባሽ?” ይላታል ትዝታ በትዕግስት በአውንታ ትመልሳለች ልጁ ግን ሊያቆም አልቻለም ትዝታም ከዛ በላይ ልትታገሰው አልቻለችም “ትዝታ…” ብሎ ንዝነዛውን ከመቀጠሉ በፊት ምርር ያለት ትዝታ ንግግሩን አቋረጠችው እና “አንተ ደግሞ ከችግሬ በላይ ጎልተህ አትታየኝ እስቲ…” ብላው እርፍ

እስክ እኛም ጋር
ከአገር በላይ ወንበራችው
ከነጻነት በላይ ክብራቸው
ከአንድነት በላይ ጽንፈኝነታቸው
ክመንጋው በላይ የግል ጥቅማችው
ከመንፈሳዊው በላይ ኢመንፈሳዊነታቸው ጎልቶ እንዲታይ/እንዲታየን የምታደርጉ ሁሉ
እስኪ ከችግራችን በላይ ጎልታችሁ አትታዩን

የትዝታ አምላክ ይገላግላን ሌላ ምን ይባላል