Sunday, December 4, 2011

አይ ድሃ መሆን መጥፎ - እንደ ሴት ልጆቻችን ወንድ ልጆቻችንን አሳልፈን ልንሰጥ ይሆን ?

አንቺ ደግሞ ምነው አበዛሸ ተሉኝ ይሆናል ግን ወድጄ አይደለም ከዚህ በፊት ኢትዮጲያ ውስጥ ‘በቀላሉ’ የገቢ ምንጭ የሆኑ ማንኛውም አይነት ሥራዎች በትክክለኛው መንገድ ኅብረተሰቡንና ሥራውን የምትሠራው/የሚሠራው ላይ  ያላቸው ተጽኖና ጉዳት ከግንምቱስጥ ሳይወሰድ እደሰደድ እሳት አገራችንን ማጥለቅለቃቸውን ሰለማስታውስ ነው።አንዱን እና ዋነኛውን ላንሳላችሁ
የድሮ ወላጆች ለልጆቻችን ምን እናወርሳለን ነበር ጭንቀታቸው ባለንበት ጊዜ ግን ገበሬውን ከእርሻው ነጋዴውን ደግሞ ከትርፉ በልቶ እንዳያድር የኑሮ ችግር ከአቅም በላይ ሆኖበታል ስለዚህ ለልጁ የሚያወርሰውን ሳይሆን ልጄ ከመቼ አድጋ በረዳችኝ የሚለው ይበልጥ ያሳሰበዋል።በዚህ መካከል ግን ረሃብን ማስትገሻ ችግርን ማሽነፊያ የኖነው አንዱ መንገድ ወደ አረብ አገር መሄድ ነበር።ሰለዚህ ክርስቲያኗም ፋጡማ ሆናና ያንገቷ ማትም በጥሳ ሂጃብ ተጠምጥማ ጉዞ ወደ አረቡ አገር፤ ራሷን ጥቅማ ከምንም በላይ ደግሞ በተሰቦችዋን በልተው እንዲያድሩ ለማድረግ።
እድል የቀናት እና የቀጣሪዋ ሚስት ቀልቧ ያልጠላት ወይም ደግሞ በቀጣሪዋ ተደጋግሞ መደፈርን ተቋቁማ መኖር ከቻለች ያሰበችውን ከግብ ታደርሳለች ይህ ካልሆነ ግን ጨካኝ አሰሪ ካጋጠማት ወይ ከደረጃ ወይ ደግሞ በመስኮት እንደ እቃ ተወረውራታለች።እንዲሁም ደግሞ አብዛኛዎቹ በህገወጥ መንገድ ሰለሚገቡ የኢትዮጲያ  አየር ማረፊያ ጎራ ካላችሁ ወይ ተጠርዛ ወይ ደግሞ በስትሬቸር እየተገፋች ከአረብ አገር የምትገባ  ሴት ማየት የተለመደ ሆንዋል። የሞቱትንና የደረሱበት የማይታወቁትን ቤት ይቁጠረው።
ይህ ግን ወደ አረብ አገር የሚሄዱት ሴት ልጆች ቁጥር አልቀነሰውም። ይልቁንም በየክሊኒኩ እና በየሆስፒታሉ የሞላው በአስራዎቹ ወስጥ ያሉ ሴት ልጆቻቸውን ይዘው የመጡ እጅግ በጣም ብዙ አባቶች ናቸው።እነዚህ ልጆች ወደ አረብ አገር ለመሄድ የሚያስፈልገውን የጤና ምርመራ እና ፎርማሊቲ በራሳቸው መጨረስ ስለማይችሉ ነው አባቶቻቸው እነሱን ይዘው ከክፍለ አገር ድረስ የሚመጡት። ይህን እራሳቸው መጨረስ ካልቻሉ ሰው አገር ሄደው ሥራ እንዴት ይሠራሉ የሚለው እንዳለ ሆኖ አባቶቻቸው በልጆቻችው ላይ እንደ ተምቦላ የእድል ጨዋታ ሲጫወቱባቸው ይገርመኛል ነገሩ ግን ምን ይደረግ ችግር ነዋ፣ ድሃ መሆን፣ ድሆች ሰለሆንን፣ የተገኘውን አጋጣሚ ተጠቅሞ በልቶ ለማደር መሞከር፣ ገንዘብ ማግኘት።
ግብረ ሰዶማዊነት ወደ አገራችን አገር ለማየት ከቱሪስቶች ጋር አብሮ ገባ።
ግብረ ሰዶማዊነት ወደ አገራችን የገባው ለተለያየ ጉዳይ ወደ አገራችን በሚመጡ የወጭ አገር ዜጐች እና ለብዙ ዓመታት በምዕራቡ ዓለም ኑረው በተመለሱና በሚመለሱ አንዳንድ ኢትዮጵያውን ጭምር መሆኑን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች የዚህ አጸያፊ ድርጊት ሰለባ የሆኑትና ሰለባ የሚያደርጉት ቀደም ሲል በእነርሱ ላይ ካለፈቃዳቸው በግብረ ሰዶማውያን ተገደው በመደፈራቸው በመሆኑ ይነገራል፡፡ በተለያዩ ጥቅማጥቅም በመታለል በተፈጸመባቸው ወሲባዊ ጥቃት የእነርሱን የሕይወት መስመር ለመከተል እንዳበቃቸው ከግብረ ሰዶማውያኑ የተገኙ መረጃዎች እንደሚጠቁሙ በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡ ግብረ ሰዶማውያኑ ዛሬ በመዲናችን በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች ኅቡዕ ድርጅት በማቋቋም፣ በካፌዎች እና በተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎች ድርጊቱን እያስፋፉ ይገኛሉ፡፡                                                                              "ወደ ሀገራችን በእነዚህ ወገኖች ታዝሎ በገባው የግብረ ሰዶም ተግባር በተለይም ዕድሜያቸው ከ10-14 በሚደርሱ የጐዳና ተዳዳሪዎች፣ በአንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እገዛ በሕፃናት ማሳደጊያ ማዕከል በሚኖሩ አዳጊዎች ላይ ሳይቀር ድርጊቱ እየተፈጸመባቸው ነው፡፡ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ሕፃናትንና ወጣቶችን ለማማለል የተለያዩ አደንዛዥ ዕፆችን፣ ከረሜላ፣ ቸኮላት መሳይ ማደንዘዣ፣ ጫት፣ አልኮል እና የሚጤስ ነገር በመጠቀም ካደነዘዙአቸው በኋላ ድርጊቱን ይፈጽሙባቸዋል፡፡ እንዲሁም ጐልማሶችን በተለያዩ መሣሪያዎች በማስፈራራት እንደሚደፍሯቸው አንድ የጥናት ወረቀት ያስረዳል፡፡ /በላይ ሐጎስ፣ "Sexual abuse and Exploition of male chidren in addis ababa" 2007/http://eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&view=article&id=1:2011-12-02-08-19-57&catid=2:-&Itemid=2"
እስካሁን በማሰገደድ ተፈጸመ ከዚህ በኋላ ግን እንደዚህ ችግር ከልዕልናችን በላይ ፈጦ ባለበት ሰዓት እና ህጻናትን የሚጠብቅ እና የሚያስጠብቅ ጥብቅ የሆነ ህግና ስርዓት በሌለበት ሁኔታ ትናንት ሴት ልጆቹን ያሰለፈ ወላጅ ወንድ ልጆቹን ለዚህ ነውር ለማሰለፍ እንደማይገደድ ምን ማረጋገጫ አለን ? 

እመ ብርሃን የአስራት አገሯን  ተጠብቅልን - አሜን

7 comments:

 1. Amen Egziabhere yemaren Dingil ateleyen.

  ReplyDelete
 2. please visit www.betepawlos.com

  ReplyDelete
 3. ትንሽ ጠለቅ ብሎ እግዜር የሰጠንን አእምሮ መጠቀም ደህና ነው።
  ግብረ ሰዶም ምንድነው? የግንኙነት ድርጊቱ ነው ወይስ በተመሳሳይ ጾታ መካከል መሆኑ ነው? ለምሳሌ..ድርጊቱ በሴትና በወንድ መካከል ቢደረግ "ግብረሰዶም" ይባላል? ተቀባይነትስ አለው ወይስ እኩል ይወገዛል?
  እነዚህ ጥያቄዎች ምክንያት አላቸው። ምክንያቱም ግብረሰዶም ድርጊቱ ከሆነ...ይህን ድርጊት ኢትዮጵያ ውስጥ ማነው ያመጣው? ፈረንጆች? በየቤቱ ጓዳ ስንቱ ድርጊቱን ያደርጋል (ባልና ሚስትም ቢሆኑ)።
  በጄ።
  ጸሃፊው ግብረሰዶም በኢትዮጵያ እንዳልነበረ የሚጠቁመውን ጥናት አልገለጸም። ግን ጽህፉ ስለምንድነው? ስለግብረሰዶም ነው ወይስ ህጻናትን የማጥቃት ወንጀል? ምክንያቱም የህጻናት አይን ለልመና ሲባል ብቻ የሚጨለምበት አገር ውስጥ ነን ያለነው። እራሳችን በራሳችን የምናጠፋው ጥፋት ድርብ እጥፍ አይደል እንዴ?

  ReplyDelete
 4. ሽርሙጥናም እንደ ገብረ ሰዶም እኩል ሃጥያት ነው። ሽርሙጥና ደግሞ ባገራችን በመቶ ሺዎች ሳይወዱ (ባብዛኛው) ሚተዳደሩበት ስራ ነው። ስለዚህ ወንድም ሆነ ሴት..ሽርሙጥና የድህነት እና መልካም ያልሆነ አስተዳደር ነጸብራቅ ስለሆነ የኢትዮጵያ ሃይማኖተኞችም ሆኑ ቤተክርስታያናት ግልጽ የሆነ የመንግስት ተቃውሞ ማሰማት ብቻ ሳይሆን መስዋእትነትንም ማስተማር አለባቸው አይደል?

  ለምሳሌ...ከዚህ አለም በሞት ስንለይ የሰራናቸው መልካም ምግባራት ብቻ ናቸው በግዜር ፊት አጋሮቻችን የሚሆኑት። ታድያ ግን ስንቴ ነው ቄሶች ተቃውመው ሲታሰሩ የምናየው? ሁሌ ግዜጠኛው ነው። ሁሌ ተማሪው ነው። የዚህን አለም እስርቤትና ህመም ከመፍራት የገነት ጥሪ አይበልጥም? ከዚህ ሁሉ ቄስ መሃከል እንዴት አንድ ያቡነ ጴጥሮስ ተከታይ ይጠፋል?

  በላይ ሃጎስ ብዙ ጻፈ። ግን ራሱ ስንት እርምጃ ተራምዶ ይሆንን? አይመስለኝም።

  ReplyDelete
 5. Mahlet,
  You woke up very late like your friends and colleagues as usual. Try to improve your jib kehede... approach please...

  ReplyDelete
  Replies
  1. Adugna ZeDebreGenetMay 26, 2012 at 11:11 AM

   ወዳጄ፡ ያንተ ጅብ ከሄደ ሌላ ጅብ እንዳይመጣብህ ራስህንና ሌሎችን መጠበቁ መልካም ነው፡፡ ጽሑፉ የሚያሳስበው ብዙ ጅቡ ያልደረሰባቸው ጭራሹንም ስላልሰሙት በአስር ሚሊዮን ስለሚቆጠሩት ወገኖች ነው፡፡ እናም መረጃው ወቅቱን የጠበቀ ነው፡፡

   Delete
 6. Mahilet,
  I wonder your article. God bless you!

  ReplyDelete