Thursday, April 21, 2011

ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ


ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ
በመስቀል ሆነህ አባት ሆይ
ድምጽን በማሰማት አባት ሆይ
ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ
ከዋክብት ከሰማይ በሙሉ ረገፉ
ጨረቃ እና ፀሐይ ደምን አጎረፉ
ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ
ሥጋህ በመስቀል ላይ ተጋልጦ ስላዩ
አዝ………
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸተጠማሁ እያለ
ማርና ወተትን ለሚመግበው
ሀሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው
አዝ…….
አካሉ ሲወጋ ደም ውኃ ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ
የገሊላ ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለነሱ አዘንክ እንጂ ላንተስ አላሰብህ
አዝ……
እናቱ ስታለቅስ በመስቀል ሥር ሆና
ዮሐንስን ሰጣት ጠብቆ እንዲያጽናና
መላእክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሰራዊት ፈርተው ተረበሹ

No comments:

Post a Comment