Monday, December 31, 2012

በክርስትና ይቅርባይነት ሁለቴ የሚታሰብበት ተግባር አይደለምለቤተ ክርስቲያንና ለክርስትና ልዩ ፍቅር እንዲያድርብኝ ያደረጉኝና በቃልም በሕይወት ያሰተማሩኝ ሰዎች ጥቂት የሚባሉ አደሉም ከነሱ መካከል ግን ትዝታቸው ሁል ጊዜ የማልረሳቸው የሰሜን ጎጃም ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት እና ከጥቂት አመታት በፊት ያረፉት አቡነ በርናባስ ናቸው:: በካንፓስ በነበረኝ ቆይታ ተማሪዎችን በእምነታቸው በማጽናትና የመንፈስ አባት በመሆን ታላቅ ሥራ የሰሩ አባት ነበሩ። እሳቸው ክርስትንና በቅዱሳን እምነት ስለቤተ ክርስቲያን ደግም በግብረ ቅዱሳን ምስክርነት ያስተምሩን ትዝ ይለኛል:: ካሰተማሩኝና በታሪኳም ቤተ ክርስቲያን ብዙ ፈተናዎች እና ተግሮቶች አሳልፋላች::ተወጥታለች::ይህ የሆነው በእግዚአብሔር ሃይል ቢሆንም የቤተ ክርስቲያን ልጆች እና አገልጋዮች ፈተናው በሚጠይቀው ዋጋ መጠን ስለከፈሉ ነው።ሕይወት እሰከመስጠት::

ፓትሪያርክ አቡነ  ጰውሎስ ካረፉ 5 ወር ሊሞላ 2 ሳምንት ቀርቷል:: በዚህ ወቅት በቤተ ክርስቲያን አባቶችም በአገልጋዮችም በምዕመኑም ዘንድ ሲታስብ የቆየው የቤተ ክርስቲያኗ አባቶች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት ነው። ይህም የሆነበት ምክኒያት ይህንን ችግር አሁን መፍታት ካተቻለና ወደ ፊት መፍትሄ ወደማይገኝለት ደረጃ እንደሚደርስ ስለሚታመን ነው።  ይህ ያሳሳባቸው ሁሉ በየበኩላቸው ብዙ ሲጣጣሩ ቆይተዋል:: ከመቸውም በላይ በነዚህ ጥቂት ወራት ወስጥ የእርቀ ሰላሙን አስፈላጊነት የሚያሳስቡ (ግድ የሚሉ) ብዙ መልእክቶች/ጽሁፎች ተጽፈዋል::በተለያዩ መንገዶችም  አገልጋዩና ምዕመኑ ድጋፉን ስገጽ ቆይቷል::

ይህንን ቅዱስ ሲኖዶስም ትኩረት በመስጠት ከዚህ በፊት ተቋቋሞ ከነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ በተጨማሪ ሌላ የዕርቀ ሰላም ልኡካን አዘጋጅቶ የእርቅ ንግግሩን ውጤታማ በሚመስል መልኩ እንዲቀጥል አድርጓል። ለዚህም ከኅዳር 26 30 ቀን 2005 . በዳላስ ቴክሳስ ለሦስተኛ ጊዜ ጉባኤ ተዘጋጅቶ ያለስምምነት በሰላም ተፈጽሟል። የሚያስማማ የመፍትሄ ላይ ላለመድረሳቸው ብዙ ምክኒያቶች አስተዋጾ አድርገዋል::

የእርቀ ሰላም ልኡካን እዚህ ሰሜን አሜሪካ ከደረሱ ጀምሮ እርቁን በተፈለገው መልኩ እንዳይካሄድ አስተዋጽኦ ያደረጉ ብዙ ነገሮች ተከስተዋል ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹን ለማስታወስ
1.      የፕሬዝዳንት ግርማ ወለደጊዮርጊስ ለቤተ ክርስቲያኗ የሚበጅ ያሉትን፣ አቡነ መርቆሪዮን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ መንበረ ፕትርክናውን እንዲረከቡ የሚጠቁም ደብዳቤ መጻፍ፣ መልሰው ደግሞ ማጠፈቸው፣ ይህን ጉዳይም አሰመልክቶ አቃቤ መንበሩ አቡነ ናትናኤል በቪኦኤ በሰጡት ምላሽእሳቸው አያገባቸውም” የኢህአዴግ መንግስትም ተቆጥቷልማለታቸው፣
2.      የእርቁ ድርድር ሳይጠናቀቅና አቢይ መፍትሄ ላይ ሳይደረስ የፓትሪያርክ አሰመራጭ ጉባኤ መቋቋሙ ይህንን አስከትሎ ደግሞ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ሂደቱን መቃዎሙ፣
3.      የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ መግላጫ ልኡካኑ ኢትዮጵያ ከመድረሳቸው መውጣቱና መግላጫውም የሰላምና አንድነት ጉባኤን አካሄድ የሚነቅፍ መሆኑ
4.      ጉዳዩ በቅርበት ለመከታተልና ልዩነቶችን በንግግር ለመፍታት ወደ ኢትዮጵያ የሄዱት የሰላምና አንድነት ጉባኤ አባል የሆኑት ሊቀ ካህናት ሃይለሥላሴ የዕርቀ ሰላም ልኡካኑ ከተመለሱ በኋላም ቢሆንም ተገደው ካገር እንዲወጡ መደረግ፣ ሌላም ሌላም

ታዲያ ይህ በእንዲህ እንዳለና የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ሰላም እንደሚያመ ተጥሎበት የነበረው የዕርቅና ሰላም ሂደት በወሳኝ ዊ ወቅት ላይ በሚገኝበት በዚህ ዓት ቅዱስ ሲኖዶስ ቀጣዩን ፓትሪያክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እደሆነ ይነገራል።

ለወደፊት ያለው አደጋ
እንደሚነገረው ቅዱስ ሲኖዶስ በአስመራች ጉባኤ አማካይነት በምርጫው ቢቀጥል ለወደፊት ለቤተ ክርስቲያኗ ሊታረም የማይችል ችግር ይገጥማታል።የመጀመሪያውና ዋነኛው ቤተክርስቲያን ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በማረፋቸው ምክንያት ሌላ ፓትሪያርክ ከሾመች በዚህ በኩል ደግሞ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ ቀናቸው ደርሶ ሲያርፉ ሌላ ፓትሪያርክ ከተሾመ የችግሩን ምክኒያት ሰለሚያበዛው ኣና ሰለያወሳስበው በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሰረት ለማሰተካከል አሰቸጋሪ ይሆናል:: በሌላ ረገድ ደግሞ የፓትሪያርክ ምርጫው ሆነ የእርቅ ሂደቱ በሁለቱም የአባቶች ወገን እንዲሁም ሰለቤተ ክርስቲያን ያገባናል የሚሉ አካላት በሙሉ በየደረጃቸው የተሳተፉበት ስለሆነ በእግዚአብሔር ፊትም በታሪክም የቀደሙት አባቶችችን በተግባር ያስተማሩን ትምህርት የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለመጠበቅ ሲባል አስፈላጊውን መስዕዋትነት ባለመክፋል ሁላችንንም ተወቃሽ ያደርገናል።

አገልጋዩና ምዕመኑ ምን ይጠብቃል
ቤተ ክርስቲያን ያዘኑት መጽናኛ ናት፣ ቤተ ክርስቲያን የተቸገሩ መጠጊያ ናት፣ቤተ ክርስቲያን ምዕመና  ሰላምን የሚያገኙበት ናት፣  ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን እምባቸው የሚታበበስበት የምህረት ቤት ናት:: ምዕመኑ ከምንም በላይ ሰላምን አንድነትን ይፈልጋል:: አሁን የተፈጠረው የአስተዳደር ችግር በሰላማዊ መንገድ እንፈታ እምም በጸሎትም እግዚአብሔርን ይማጸናል:: አገልጋዩና ምእመኑ ሳይቆርጥ ካባቶች ጎን በመቆም ባቶች ላይ የለውን እምነት አሳይቷል:: በተለይ ደግሞ በአባቶች መለያየት ቀጥተኛ ተጠቂ የሆነው በዲያጶራ የለው ምዕመን እርቁን ከምንም በላይ ስለሚፈልገው የአቅሙን ሲያደግ ቆይቷል::
አገልጋዩና ምዕመኑ የተጀመረው የእርቀ ሰላም ሂደት የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና እና በወቅቱ የነበረውን ታሪካዊ እውነታ መሠረት ባደረገና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ለቀጣዩ የቤተ ክርስቲያንን ተረካቢ ትውልድ ሲባል የማያዳግም የመጨረሻ መፍትሄ እንዲያገኝ ይጠብቃል:: ቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ሌሎቹም አባቶች ቂመኝነትን አለመስማማትን በእርቅና በመግባባት አጥፍተው ልባቸውን ለፍቅር ለሰላም ለርህራሄ ክፍት እንዲያደርጉ ይጠብቃል:: አባቶች መንግስትንም ጨምሮ ያለምንም ውጫዊ ተጽኖ በፈሪሃ እግዚአብሔር በርጋታ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ ይጠብቃል:: 

ማንን ተስፋ እናድርግ ?
የባቢሎን ንጉስ ናቡከደነፆር አናንያን አዛሪያን ሚሳኤልን አምላኬን ለምን አለማምለካችሁም ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል ለምን አለመስገዳችሁም ብሎ በጠየቃቸው ሰዓት እንዲህ ብለው መለሱለት “ናቡከደነፆር ሆይ፥ በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም። የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፥ ንጉሥ ሆይ! ነገር ግን፥ ንጉሥ ሆይ፥ እርሱ ባያድነን፥ አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ” አሉት።
ከሁሉም በፊት ልዑል እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግ እርሱን ታምኖ በእምነት መቆም ያስፈልጋል:: በተጨማሪ የሚሆነው ሁሉ እግዚአብሔር የፈቀደው ቢሆንም እንደ ሰልስቱ ደቂቅ እውነትን እውነት ትክክል ያልሆነውን ደግሞ ሃሰት ማለት ያሰፈልጋል:: በቅናት መንፈስ ለቤተክርስቲያን ዘብ መቆም አማኙን ለሚያስ እንደ ናቡከደነሶ ለጣዖት አሰጋጅ ብቻ ሳይሆን ለነገው የቤተ ክርስቲያን ተረካቢም ትውልድ የሚያሰብ ሃላፊነት ከሚሰማው ሁሉ የሚጠበቅ ነው::

አምላከ ቅዱሳን ቸር ያሰማን